1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቐለ በረራ ጀመረ

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 19 2015

የኢትዮጵያ አየር መንገድ መደበኛ የመንገደኞች አውሮፕላን ዛሬ ከቀኑ7 ሰዓት ላይ መቐለ ደርሷል። ከ18 ወራት በኋላ ዛሬ 138 ተጓዦችን ይዞ መቀሌ የገባው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ከመቀሌም መንገደኞችን ጭኖ ወደ አዲስ አበባ ተመልሷል። ዶቼቬለ ያነጋገራቸው መንገደኞች በአገልግሎቱ መጀመር መደሰታቸውን ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/4LUqS
Äthiopien Der erste Flieger landete regionalen
ምስል Million Haileselassie/DW

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቐለ በረራ ጀመረ


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ18 ወራት በኃላ ዛሬ ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ እንዲሁም ከመቐሌ ወደ አዲስ አበባ መደበኛ የመንገደኞች የአውሮፕላን በረራ አገልግሎት ጀመረ። የመጀመሪያው የኢትዮጵያ አየር መንገድ መደበኛ የመንገደኞች አውሮፕላን ዛሬ ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ መቐለ ደርሷል ። አልፎ አልፎ የሚደረግ የረድኤት ድርጅቶች በረራ ከማስተናገድ በስተቀር ከስራ ውጭ ሆኖ የቆየው የመቐለው አሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፍያ ዛሬ 138 ተጓዦች የጫነ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላንን ተቀብሏል። አውሮፕላኑ ከመቀሌ መንገደኞችን ጭኖ ወደ አዲስ አበባም ተመልሷል። የኢትዮጵያ መንግሥትና ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ(ህወሓት) ፕሪቶሪያ ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ የሰላም ስምምነት በተፈራረሙ ሁለት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የተጀመረው በረራ በጦርነቱ ምክንያት የተለያዩ ቤተሰቦችን አገናኝቷል። ዶቼቬለ ያነጋገራቸው መንገደኞች በአገልግሎቱ መጀመር የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል። የበረራዎቹ ቁጥር እንዲጨምርም ጠይቀዋል።ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ ዝርዝር ዘገባ አለው። 
ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ 
ኂሩት መለሰ
እሸቴ በቀለ