1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ውሳጣዊ ጥንካሬ እና የውጪው ጫና

እሑድ፣ ሐምሌ 24 2014

የኢትዮጵያ ውስጣዊ የፖለቲካ ሁኔታ ባልተረጋጋበት፤ ውጊያ፤ ግጭት እና ጥቃት በሚታይበት አጋጣሚ ለውጭ ኃይሎች ጫና እና ወረራ መጋለጧ ይደጋገማል። በቅርብ ዓመታት የሰሜን ኢትዮጵውን ጦርነት ተከትሎ የሱዳን ኃይሎች ድንበር አልፈው የመግባታቸው ርምጃ ታይቷል።

https://p.dw.com/p/4EtAa
Karte Äthiopien englisch

እንወያይ

የኢትዮጵያ ውስጣዊ የፖለቲካ ሁኔታ ባልተረጋጋበት፤ ውጊያ፤ ግጭት እና ጥቃት በሚታይበት አጋጣሚ ለውጭ ኃይሎች ጫና እና ወረራ መጋለጧ ይደጋገማል። በቅርብ ዓመታት የሰሜን ኢትዮጵውን ጦርነት ተከትሎ የሱዳን ኃይሎች ድንበር አልፈው የመግባታቸው ርምጃ ታይቷል። በአሁኑ ጊዜ ደግሞ ሶማሊያ ውስጥ መሠረቱን ያደረገው ዓለም አቀፍ አሸባሪ ቡድን አሸባብ ድንበር ዘልቆ በምሥራቅ ኢትዮጵያ በኩል ጥቃት እያደረሰ መሆኑ እየተነገረ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናትም የቡድኑ ጥቃት በአጸፋ ጥቃት መቀልበሱን እየገለጹ ነው። ከጎርጎሪዮሳዊው 2006 ዓ,ም አንስቶ አሸባብ በሶማሊያ ሲንቀሳቀስ በሌሎች አጎራባች ሃገራት ላይ ጥቃቶችን ሲፈጥም ኢትዮጵያ ላይ ያሰባቸው ሙከራዎች መክሸፋቸው ሲነገር ቆይቷል። አሁን ለምን ቡድኑ የተጠናከረ ጥቃት ለመክፈት ተነሳ ለሚለው የተለያዩ ሃሳቦች ይነሳሉ። በሀገሪቱ ውስጥ የሚታየውን ያልተረጋጋ የጸጥታ ሁኔታን ተጠቅሞ ሊሆን እንደሚችል ሲናገሩ እንዳሉ ሁሉ ሀገር ውስጥ የጦር መሣሪያ አንሥተው ከሚዋጉ ኃይሎች ጋር ተቀናጅቶ ቢሆን ነው የሚል ግምት የሚሰነዝሩም አሉ። ጉዳዩን በአባይ ወንዝ ምክንኢት ከኢትዮጵያ ጋር የምትወዛገበው ግብጽ እጅ አለበት በሚል የሚሞግቱም አሉ። ዶቼ ቬለ የኢትዮጵያ ውስጣዊ ጥንካሬ እና የውጪው ጫና እንዴት ይታያል? መውጫ መንገዱስ? በሚል ውይይት አካሂዷል። ሙሉ ውይይቱን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ። 

 ሸዋዬ ለገሠ