የኢትዮጵያ የሕንጻዎች የርዕደ መሬት ኮድና አተገባበሩ
ሐሙስ፣ የካቲት 2 2015በደቡባዊ ቱርክ እና ሶርያ ድንበር አካባቢ ከደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ የሟቾች ቁጥር ከ19 ሺህ ማለፉን ተገልጿል። በሬክተር መለኪያ 7.8 እና 7.5የተመዘገቡት እነዚህ በአስር ሺዎችን የሚቆጠሩት ላይ ጉዳት አድርሷል። የቱርካይ ፕሬዝደንት ረሲፕ ጠይብ ኤርዶኻን በአደጋው ከ85 ሚሊየን የቱርክ ሕዝብ 13 ሚሊየኑ መጎዳቱን በማመልከት በ10 የቱርክ ክፍለ ሃገራት የአስቸኳይ ጊዜ ደንግገዋል።
በኢትዮጵያ የሰምጥ ሸለቆንና የዳሉል እሳተገሞራ አካባቢና አጎራባቾች ላይ በየጊዜው የሚነሱ የመሬት መንቀጥቀጦች የከፋ ጉዳት ባያደርሱም የጥንቃቄ ደወልን የሚደውሉ ናቸው። በመሬት መንቀጥቀጥ የሚመጣው ተፈጥሮአዊ አደጋ ማስወገድ ባይቻልም ሕንጻዎች ለዚህ በሚስማማ መልኩ በመገንባት ግን አደጋውን መቀነስ እንደሚቻል የመስኩ ባለሙያዎች ይገልጻሉ። ለመሆኑ በኢትዮጵያ የግንባታ ሂደት የርዕረ መሬትን ጉዳት ለመቀነስ የሚያስችል ስርዓት አለ ወይ ስንል በሙያቸውም ስቪል መሃንዲስና
በሐረማያ ዩኒበርስቲ የቴክኖሎጂ ኢኒስቲትዩት ማነጂንግ ዳይሬክተር እንዲሁም የሁለተኛ ዲግሪያቸውን በርዕደ መሬት ላይ የሰሩት አቶ ሃምዛ አሕመድ ኑርን አነጋግረናቸዋል።
«በሐገራችን ከአውሮፓውያኑ የተቀዳ የርዕደ መሬት ኮድ አለ። ጥያቄው ተግባራዊ እየነ ነው ወይ ነው።»
ባለሙያው አቶ ሃምዛ እንዳሉት ሕጉ ቢኖርም በተለያዩ ሁኔታዎች ግን እየተተገበረ እንዳይደለና አይበለውና አደጋ ከደረሰ ጉዳቱ የከፋ እንደሆነ እስጠንቅቀዋል።
«ርዕደ መሬት የተፈጥሮ አደጋ በመሆኑ ማስወገድ አይቻልም። የሚደርሰውን አደጋ መቀነስ ግን ይቻላል። በመሆኑም ሕንጻ ሲሰረ ከንድፉ ጀምሮ ይህን ታሳቢ ሊሆን ይገባል። ካልሆነ ግን የሚደርሰውን አደጋ መገመት አይቻልም።»
ከሰማይ ጠቀስ ሕንጻዎች ጋር ተያይዞ ሌላው የሚከሰት አደጋ መብረቅ ነው። በአገራችን በለይም በዋና ዋና ከተሞችና በግዙፍ ፕሮጀክቶች የመብረቅ መከላከያ ንድፎች ጅማሮዎች የነበሩ ቢሆንም በተለይ በግል በሚገነቡ ሕንጻዎች አሁን አሁን እየተተወ እንደሆነ የኤሌክትሪካል ምህንድስና ከፍተኛ መሃንዲስ ኢንጅነር አንተነህ ታየ አጫውተውናል።
ሁለቱ ባለሙያዎች የርዕረ መሬትና የመብረቅ መከላከያዎች ንድፍ ተግባራዊ መደረግ እንዳለበትና የሚመለከታቸው አካላትም ሕጉን በማስፈጸም በኩል የሚታየውን ግድፈት እንዲያርሙ አሳስበዋል።
ዮሐንስ ገብረእግዚአብሄር
እሸቴ በቀለ