1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ጦር ተመልሶ ሶማሊያ ገባ ተባለ

ማክሰኞ፣ ጥር 26 2001

በፌርፌር አካባቢ የሚገኙ አንዳንድ ነዋሪዎች እንደገለፁት፤ የኢትዮጵያ ወታደሮች በአካባቢው የፍተሻ ጣቢያ አቓቁመው ተሽከርካሪዎችን እየተቆጣጠሩ ነው። በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ የምትገኘው የበለድወይኔ ነዋሪዎች በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ ወታደሮች ድንበር ዘልቀው ሃያ ኪሎ ሜትር ገብተዋል ሲሉ ለሮይተር እማኝነታቸውን ገልፀዋል።

https://p.dw.com/p/GmQm
የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሼክ ሸሪፍ ሼክ አህመድ
የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሼክ ሸሪፍ ሼክ አህመድምስል AP

ኢትዮጵያ ጦሯን ሙሉ ለሙሉ ከሶማሊያ ማስወጣቷን በገለፀች በጥቂት ቀናት ውስጥ ተመልሳ ወደ ሶማሊያ መግባቷን አንዳንድ የዜና ምንጮች እማኞችን በመጥቀስ ዛሬ ዘገቡ። የኢትዮጵያ የመገናኛ ወይንም የኮሚኒኬሽን ሚንስትር አቶ በረከት ስምኦን “ይህ መሰረተ ቢስ መረጃ ነው” ሲሉ ዛሬ ለዶቸቬለ በሰጡት ቃለመጠይቅ አስተባብለዋል። ኢትዮጵያ ወደ ሶማሊያ ተመልሳ ከገባች ሁኔታው አሳሳቢ እንደሚሆን በለንደን የቻተም ሀውስ የአፍሪቃ ቀንድ ጉዳይ ተንታኟ ሚስ ሳሊ ሂሊ ገልፀዋል።

Mantegaftot Silshi

Negash Mohammed