በደቡብ አፍሪቃ የዉጭ ዜጎች ይዉሉልን የሚለዉ ተቃዉሞ አይሏል፤
ዓርብ፣ የካቲት 17 2009ማስታወቂያ
ዛሬ ወደ ሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ያመራ በነበረው ሰልፍ ላይ ከተካፈሉት አንዳንዶቹ ዱላ ይዘው ነበር። ጥላቻን ያንጸባርቅ የነበረው ይህ ሰልፍ መፈቀድ አልነበረበትም ሲል በኔልሰን ማንዴላ ስም የሚጠራው ድርጅት ወቅሷል። ሥራ አጥነት ከ25 በመቶ በላይ በሆነበት በደቡብ አፍሪቃ የውጭ ዜጎች የሀገሪውን ሥራ እየወሰዱ ነው የሚሉ ክሶች ተደጋግመው ይቀርባሉ። በዛሬዉ ዕለትም የዉጭ ዙጎች ከሀገሪቱ ይዉጡ የሚሉ ሰልፎች የተካሄዱ ሲሆን ፖሊስ ሰልፉን በመበተን ሥራ ተጠምዶ ተሰምቷል። ደቡብ አፍሪቃ ዉስጥ የሚገኙ የዉጭ ዜጎች ይዉጡ የሚለዉን ሰልፍ የተቃወመ ሰልፍም ተካሂዷል። በዚህ መካከልም የዉጭ ዜጎች ንብረቶች የሆኑ በርካታ ሱቆች ተዘግተዉ መዋላቸዉን ጆሃንስበርግ የሚገኘዉ ዘጋቢያችን መላኩ አየለ ገልጾልናል።
መላኩ አየለ
ሸዋዬ ለገሠ