Eshete Bekeleማክሰኞ፣ የካቲት 13 2010የኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ እንዳሳሰባት ጀርመን ገለጸች። የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ "የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በኢትዮጵያ መደንገግ የሰብዓዊ መብቶችን ይገድባል" ብሏል፤ ከወር በላይ በደቡብ ሱዳን አማፅያን ቁጥጥር ሥር የቆዩ ሁለት የኬንያ የአውሮፕላን አብራሪዎች ተለቀቁ፤ የሶማሊያ መንግሥት አዳዲስ የፖሊስ እና የስለላ መሥሪያ ቤት ኃላፊዎችን ሾመ፤ የሊቢያ የባሕር በር ጥበቃ ኃይል 441 ስደተኞችን ከባሕር መታደጉን አስታወቀ፤ የሶርያ መንግሥት ደጋፊ ኃይሎች በአገሪቱ ምሥራቃዊ ክፍል በሚገኘው ጎታ በፈጸሙት ድብደባ በዛሬው ዕለት ብቻ ቢያንስ 50 ሰዎች ተገደሉ።