«የዘጠኝ ወር ደሞዛችን አልተከፈለንም» የአዋሽ ወልድያ ሀራ ገበያ የባቡር ፕሮጀክት ሰራተኞች
ሰኞ፣ ታኅሣሥ 7 20171.7 ቢልዮን የአሜሪካ ዶላር ወጭ የተደረገበት የአዋሽ ኮምቦልቻ ወልድያ ሀራ ገበያ የባቡር መስመር ግንባታ ላይ ይሰሩ የነበሩ 3500 የሚደርሱ ሰራተኞች ደመወዝ እንዳልተከፈላቸዉ ገለፁ
ግንባታዉ በቱርኩ ስራ ተቋራጭ ያፒ መርከዚ ኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ ኮርፖሬሽን ሲከናወን የነበረ ሲሆን ከሰሜኑ ጦርነት ጋር በተያያዘ በመቋረጡ በተለይም በጥበቃ ስራ ተሰማርተዉ የነበሩ ሰራተኞች ደመወዛቸዉን በወቅቱ ሊከፈሉ እንዳልቻሉ ይናገራሉ አስተያየታቸዉን ለዶቼቬለ የተናገሩት የጥበቃ ሰራተኛ የዘጠኝ ወራት ደመወዝ እንዳልተከፈላቸዉ ገልፀዉ በርካታ ሰራተኞች ሌላ የስራ አማራጭ ፍለጋ እንደለቀቁ ይናገራሉ።
10 ጣቢያዎች፤10 ኪ.ሜ ርዝመት ያላቸው 12 ዋሻዎች፤52 የተለያዩ ርዝመት ያላቸው ድልድዮች፤ 8 የሀይል መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች፤(ሰብስቴሽንስ)፤12 የሬዲዮ ምሰሶዎች፤ አንድ የጥገና ማእከል ያሉት፡፡የአዋሽ-ኮምቦልቻ ባቡር ፕሮጀክት ባለፉት አመታት ከፍተኛ የሆነ ስርቆት እንደተፈፀመበት የጥበቃ ሰራተኞቹ ይናገራሉ .በተለይም በባቡር መስመሩ ላይ የሚፈፀም ዝርፊያ ምሽትን ተገን በማድረግ የሚፈፀም ሲሆን የተደራጁ ቡድኖች ይከናወናል።
ሌላዉ ለዶቼ ቬለ ሀሳባቸዉን ያጋሩት አቶ አንተነህ አሊ ከባቡር ፕሮጀክቱ የተዘረፉ እቃዎችን በአገለገለ ስም መሸጥ እየተለመደ መጥቷል ያሉ ሲሆን የባቡር ሀዲዱም ለአደጋ ተጋልጧል ይላሉ
የባቡር መስመር ዝርጋታዉ 11ቀበሌዎቹን የሚያቋርጥበት በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን አስተዳደር የጂሌ ጥሙጋ ወረዳ ፖሊስ ፅፈት ቤት ኃላፊ ኮማንደር መሀመድ አሊ እንደሚገልፁት ዝርፊያዉ በተሽከርካሪ የታገዘና የሰለጠኑ ሰዎች የሚፈፅሙት በመሆኑ በሀገር ሀብት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ያደርሳል ይላሉ ይሁን እንጂ በዋናነት ለዝርፊያዉ መባባስ ለጥበቃዎቹ ክፍያ የሚፈፅመዉ የቢራሮ ሴኩዮሪቲ ኤጀንሲ ክፍያዉን በጊዜ አለመፈፀሙ ምክንያት ነዉ ሲሉ ነው የሚናገሩት።
የቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ምን ይዞ መጣ ?
392 ኪሎሜትር የባቡር መሰረተ ልማት ለመጠበቅ 3500 ሰራተኞችን ቀጥሮ ያፒ መርከዚ ጋር ውል የወሰደው የቢራሮ የሴኩሪቲ ኤጀንሲ ዋና ሀላፊ አቶ አህመድ ሰይድ የኢትዮጽያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የአዋሽ ኮምቦልቻ ወልድያ ሀራ ገበያ ፐሮጀክት ጽህፈት ቤት በውላችን መሰረት መክፈል ያለበትን 100 ሚልየን ብር ሰላልከፈለ ለሰራተኛ መክፍልም ሆነ ሀብቱን መጠበቅ አልቻልንም ይላሉ።1.7 ቢልዮን የአሜሪካ ዶላር ወጭ ተደርጎበት የተሰራው የባቡር መሰረተ ልማት አሁን ላይ ምንም አይነት አገልግሎት ባለመስጠቱ ለዝርፊያ እተጋለጠ ነው የሚሉት አቶ አህመድ ሰይድ እኛም በህጋዊ መንገድ ውላችንን አቑርጠናል ይላሉ። በዚህ ዜና ላይ የኢትዮጽያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የአዋሽ ኮምቦልቻ ወልድያ ሀራ ገበያ ፐሮጀክት ጽህፈት ቤት የስራ ኃላፊዎችን ለማካተት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።
ኢሳያስ ገላው
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ