የምግብ እርዳታ መርሃግብር ለኢትዮጵያውያን ህጻናት እና እናቶች
ሰኞ፣ ሰኔ 22 2012ማስታወቂያ
የተባበሩት መንግሥታት የሕጻናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ እና የዓለም የምግብ ፕሮግራም "WFP" በኢትዮጵያ ለከፍተኛ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ለተጋለጡ ከ 4.5 ሚልዮን ለሚልቁ ሕጻናት ነፍሰጡሮችና አጥቢ እናቶች የሚደግፍ መርሃግብር በጣምራ መጀመራቸውን አስታወቁ:: በኢትዮጵያ የዩኒሴፍ አስተባባሪ ሚስ አደል ኮደር በተለይ ለዶይቼ ቨለ "DW" እንደገለፁት በአሁኑ ወቅት በኮቪድ-19 እና የምግብ ሰብልን በሚያወድመው የበረሃ አንበጣ ወረርሽኞች መስፋፋት ምክንያት ለከፋ የምግብ እጥረት በተጋለጡ 100 የተለያዩ ወረዳዎች በዝቅተኛ ኖሮ የሚገኙ ዜጎችን በጊዜያዊነት ለመርዳት ድርጅቶቹ በዓመት 35 ሚልዮን ዶላር በጀት መድበው እንቅስቃሴ ጀምረዋል::ተማሪዎች በትምህርት ገበታ ውጤታማ እንዲሆኑም በ 600 ያህል ትምህርት ቤቶች ችግረኛ ተማሪዎችን የመመገብ ዕቅድ ይከናወናል ነው ያሉት ሃላፊዋ:: ዝርዝሩን የፍራንክፈርቱ ወኪላችን እንዳልካቸው ፈቃደ አጠናቅሮታል::
እንዳልካቸው ፈቃደ
ኂሩት መለሰ
እሸቴ በቀለ