ሐሙስ፣ ኅዳር 22 2009
የጋዳ ስረዓት የባህል፣ የፖለትካ፣ የእኮኖሚና ሌሎች የማህበረሰቡን እንቅስቃሴዎች አቅጣጫ የሚያስይዝ ነው ይላሉ ስለ ገዳ ስረዓት ላይ መረጃ የሚሰበስቡት አቶ ገረሱ ቱፋ። የገዳ ስነ ስረዓትን ለማስመዝገብ እንደ ቅድመ ሁኔታ የተቀመጠዉም ለትውልድ ቢተላልፍ ጠቃሚ በመሆኑ ነዉ ሲሉ ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል።
የገዳ ስረዓት ከተወሰኑ አጥኝዎች ዉጭ በቅ ትኩረት አለገኘም ይላሉ አቶ ገራሱ።
በጋዳ ስርዓት ስልጣን የሚሸጋገረዉ ምርጫ ተካሄዶ ግልፅ በሆነ መንገድ እንደሆነ እና ግልጽ መተደደርያ ህጎችም አሉት ያሉን በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የምዕራብ ጉጂ ዞን ቡሌ ሆራ አከባቢ ተወካይ አቶ ቦናያ ሁዴሳ ናቸዉ። የገዳ ስረዓት ከአሁኑ ዘመናዊ አስተዳደር ጋር የሚያመሳስለዉ አለ ይላሉ አቶ ቦናያ።
አባ ጋዳ ማለት «አገርን የሚያስተዳድር፣ የምህረት አባት፣ የተጣሉትን ሰዎች የሚያስታርቅ፣ የሰላም አባት ማለት ነዉ ያሉኝ አሁን በጋዳ ስልጣን ላይ ያሉት አባ ጋዳ ጅሎ ናቸዉ። ባለፈዉ ዓመት የአባ ጋዳነት ስልጣን የተረከቡት አባ ጋዳ ጂሎ ላለፉት 20 ዓመታት የገዳን ስረዓት በዩኔስኮ ለማስመዝገብ ስታጋሉ እንደነበር ተናግረው ስረዓት መመዝገቡን እንዳስደሰታቸዉ ለዶቼቬሌ ይናገራሉ።
«የጋዳን ስረዓት ለየት የሚያደርገዉ የሥልጣን ሽግግሩ ድሞክራሲያዊ መሆኑ ነዉ። አንድ ቀን ወይም አንድ ወር ሳያሳልፍ በየስምንት ዓመቱ የስልጣን ርክክብ አለ። ይህ የሰለም ሽግግር ሲደረግ አባ ገዳዎች እርስ በርስ ይመራረቃሉ ። ሲመራረቁም «ወተት አጣፍጥልን፣ ማር ታፋጭ አድርግልን፣ እኔ አንተን አስተዳድሪሀለሁ አንተ ደግሞ እኔን አስተዳረኝ ኢያለ በመመረቅ ስልጣን በሰለም ስለምንረካከብ ኬሌሎች ስረዓቶች ይለያል። ቀጥሎ የሚመጣ አባ ጋዳ ሥልጣኑን የምረከብበት ቀንና ዓመተ ምህረቱን ያዉቀዋል። ለስልጣን ርክክቡ ኢሱም ተዘጋጅቶዋል እኔም ዚግጁ ነኝ አንድ ቀን ሳላሳልፍ ለተከታዩ አባ ጋዳ ለመስጠት።»
ይህ የዩኔስኮ ዉሳኔ ለህዝቡም ሆነ ለአገሪቱ ጠቀሜታዉ ምን ሊሆን ይችላልብለን የፌስቡክ ተከታታዮቻችን ጠይቀን ነበር። አስተያየታቸዉን ካጋሩን ዉስጥ «የገዳ ስርዓት መመዝገቡ ጥሩ ነው፤ ግቡ ደግሞ የቱሪስት ፍሰት ነው» ያሉን ሲኖሩ፣ ሌሎች ደግሞ «ይህ ትልቅ እድል ብቻ ሳይሆን ትልቅ ማንነትን ማስመስከሪያችን ነው። እውነት የገዳ ስርዓትን በውል ተገንዝበን በጥልቀት መርምረን መሻሻል ያለበትን አሻሽለን ብንጠቀምበት ከገዳ ስርዓት የበለጠ ድሞክራሲያዊ ስርዓት የለም ነበር፣ ያሉን አሉ።
መርጋ ዮናስ
ሒሩት መለሰ