«የጥላቻ እና የፍቅር ቃላት» ድራማ፥ ክፍል 10
እሑድ፣ ሐምሌ 26 2012ማስታወቂያ
የጥላቻ እና የፍቅር ቃላት በሚል ዐቢይ ርእስ ሲቀርብላችሁ የነበረው ተከታታይ የራዲዮ ድራማ ዐሥረኛ እና የመጨረሻው ክፍል ተጀመረ። ይኸ የወንጀል ተፋላሚዎቹ ድራማ በጎሳ ትንቅንቅ እና በጥላቻ ንግግር ላይ ያተኮረ ነው። ባለፈው ሳምንት እንደምታስታውሱት ዋና ኢንስፔክተር ኦፓንዴ የማለለለፓ ምክትል-ሊቀመንበር ባንኩን ገዳይ በቁጥጥር ሥር አውለዋል። ሳሎሜ በእርግጥም በቅናት ተነሳስታ ባንኩን መግደሏን ለፓርቲው ሊቀ-መንበር አምናለች። በስተመጨረሻ ፍትኅ ሊገኝ ይሆን? ሳሎሜ እና የቲሪቤ ወጣቶች ፍርድ ቤት ናቸው። አሁን በቀጥታ ዳኛ ኔኬሳ ወደሚመሩት ችሎት እናምራ። የዐሥረኛው ክፍል ርስስ «አገርን ማዳን» ይሰኛል።
ደራሲ፦ ክሪስፒን ምዋኪዱ
አዘጋጅ፦ ማንተጋፍቶት ስለሺ