1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«የጥላቻ እና የፍቅር ቃላት» ድራማ፥ ክፍል 9

እሑድ፣ ሐምሌ 19 2012

የወንጀል ተፋላሚዎቹ ተከታታይ የራዲዮ ድራማ ሊጠናቀቅ ሁለት ክፍሎች ብቻ ቀርተዋል። «የጥላቻ እና የፍቅር ቃላት» በሚል ዐቢይ ርእስ የሚቀርብላችሁ የዚህ ድራማ ዘጠነኛ ክፍል እነሆ ተጀመረ።

https://p.dw.com/p/3fwLB
DW Crime Fighters Serienmotiv „Our tongue, our land“

«የጥላቻ እና የፍቅር ቃላት»

ባለፈው ሳምንት ከዊላ ጥቆማ የደረሳቸው ኢንስፔክተር ኦፓንዴ የበቀል ጥቃት ለመፈጸም በዝግጅት ላይ የነበሩ የቲሪቤ ጎሳ አባል ወጣቶችን በቁጥጥር ሥር አውለዋል። እስካሁን ድረስ ግን ኢንስፔክተሩ የታዋቂዋ ፖለቲከኛዋ ባንኩ ሙቱምባን ገዳይ ለመያዝ በሚያደርጉት ምርመራ እዚህ ግባ የሚባል ውጤት አላስመዘገቡም። ያም በመኾኑ ለምርመራቸው የሚያግዝ አንዳች አዲስ ፍንጭ ያጡት ኢንስፔክተር ኦፓንዴ ተስፋ ወደመቁረጡ የተቃረቡ ይመስላል። ዛሬ ከባልደረባቸው ኢንስፔክተር ኒምሮድ ጋር በመሆን በእጃቸው ያሉ መረጃዎችን ፈትሸው ፍንጭ ለማግኘት ከቢሯቸው ተቀምጠዋል። «ትክክለኛው ወንጀለኛ»የሚል ርእስ የተሰጠው የዘጠነኛው ክፍል እንድታደምጡ ግብዛችን ነው። መልካም ቆይታ!


ደራሲ፦ ክሪስፒን ምዋኪዱ
አዘጋጅ፦ ማንተጋፍቶት ስለሺ