ጀርመን ሽቱትጋርት ውስጥ ደማቁ ድባብ ጨዋታው ከመጀመሩ በፊት
ዓርብ፣ ሰኔ 28 2016ማስታወቂያ
ጀርመን ሽቱትጋርት ውስጥ ደማቁ ድባብ ጨዋታው ከመጀመሩ በፊት
ለፍፃሜ የተጠበቁት በሩብ ፍፃሜ ሊፋለሙ ነው
በጥንታዊቱና ታሪካዊቱ ሽቱትጋርት ከተማ ጀርመን እና ስፔን ከጥቂት ሰአታት በኋላ ወደ ግማሽ ፍፃሜው ለመግባት ይፋለማሉ ። የጀርመን እና የስፔን ብሔራዊ የእግር ኳስ ደጋፊዎች ከወዲሁ የተሟሟቁ ይመስላል ። በተለይ የጀርመን ደጋፊዎች በኮይኒግ ሽትራሰ ተሰባስበው እጅግ በደመቀ ሁኔታ ድጋፋቸውን ከወዲሁ እየገለጡ ነው ። «ወደ ቤርሊን እንጓዛለን» ሲሉም በተደጋጋሚ በጀርመንኛ ሲዘምሩ ተደምጠዋል።
የ2016 ዓ.ም የአውሮፓ ዋንጫ መክፈቻ እና የጀርመን ድል
ቤርሊን የዋንጫ ጨዋታ የሚደረግባት ከተማ ናት ። ዛሬ ሽቱትጋርት አሬና ውስጥ ከምሽቱ አንድ ሰአት በሚጀምረው የሩብ ፍፃሜ ግጥሚያ ለመታደም ደጋፊዎች ወደ ከተማዪቱ እየተመመሙ ነው ።
ብዙዎች በዛሬው ግጥሚያ በምድብ ማጣሪያው አንድም ግብ ያልተቆጠረበት የስፔን ቡድን ያሸንፋል ሲሉ ገምተዋል ። የጀርመን ቡድን የዛሬውን የሩብ ፍፃሜ ካሸነፈ ዋንጫው ቤርሊን ውስጥ ይቀራል ሲሉም አክለዋል ።
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ታምራት ዲንሳ
ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር