1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጆሐንስበርግ-የብሪክስ ጉባኤተኞች አዳዲስ አባላት ይቀበሉ ይሆናል

ረቡዕ፣ ነሐሴ 17 2015

ብራዚል፣ሩሲያ፣ሕንድ፣ቻይናና ደቡብ አፍሪቃን በአባልነት የሚያስተናብረዉ ማሕበር አባል ለመሆን ኢትዮጵያ፣ ሳዑዲ አረቢያና ኢራንን ጨምሮ በርካታ ሐገራት አመልክተዋል

https://p.dw.com/p/4VW3J

ጁሐንስበርግ-ደቡብ አፍሪቃ ዉስጥ የተሰየመዉ የBIRICS አባል ሐገራት የመሪዎች ጉባኤ ማሕበሩ አዳዲስ አባላትን የሚቀበልበትን ሥልት እንደሚያፀድቅ አስታወቀ።ብራዚል፣ሩሲያ፣ሕንድ፣ቻይናና ደቡብ አፍሪቃን በአባልነት የሚያስተናብረዉ ማሕበር አባል ለመሆን ኢትዮጵያ፣ ሳዑዲ አረቢያና ኢራንን ጨምሮ በርካታ ሐገራት አመልክተዋል።ትናንት የተጀመረዉን የBIRICS ጉባኤን የምታስተናግደዉ ደቡብ አፍሪቃ ዛሬ እንዳስታወቀችዉ ማሕበሩ አዳዲስ አባላትን የሚቀበልበትን ሥልትና መመዘኛ ለመወሰን ጉባኤተኞች ተስማምተዋል።የደቡብ አፍሪቃ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ናሌንዲ ፓንዶር ዛሬ እንዳሉት ጉባኤተኞቹ ማሕበራቸዉ ተጨማሪ አባላትን እንዲቀበል ተስማምተዋል። የአባልነት መመዘኛ፣ ስልትና ቅድሚያ የሚሰጣቸዉን አመልካቾችንም ጉባኤዉ ከመጠናቀቁ በፊት በይፋ ያስታዉቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።በጁሐንስበርጉ ጉባኤ ላይ የሩሲያዉ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን በአካል አልተገኙም።በርቀት ግን በበይነ-መረብ ጉባኤዉን እየተካፈሉ ነዉ።