1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

"ሄር ሂሴ" - የሶማሌ ዒሳ ማህበረሰብ ባህል በዩኔስኮ ተመዘገበ

ሰኞ፣ ኅዳር 30 2017

የሶማሌ ዒሳ ማህበረሰብ የሚመራበት ያልተፃፈ ባህላዊ ህግ "ሄር ሂሴ" በዓለም አቀፉ የትምህርት፤ የሳይንስና ባህል ተቋም «ዩኔስኮ» በሰው ልጆች ወካይ የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ ተመዝግቧል። ማህበረሰቡ የሚገኝባቸው ኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ እና ሶማሊያ በጋራ በኢትዮጵያ አስተባባሪነት ባዘጋጁት ሰነድ ያቀረቡት የቅርስ ይመዝገብልን ጥያቄ አዎንታዊ ውሳኔ አግኝቷል።

https://p.dw.com/p/4nuuR
ዓለም አቀፉ የትምህርት፤ የሳይንስና ባህል ተቋም «ዩኔስኮ»
ዓለም አቀፉ የትምህርት፤ የሳይንስና ባህል ተቋም «ዩኔስኮ»ምስል Alain Jocard/AFP/dpa/picture alliance

"ሄር ሂሴ" - የሶማሌ ዒሳ ማህበረሰብ ባህል በዩኔስኮ ተመዘገበ

የሶማሌ ዒሳ ማህበረሰብ የሚመራበት ያልተፃፈ ባህላዊ ህግ የሆነው "ሄር ሂሴ" በዓለም አቀፉ የትምህርት ፣ የሳይንስ እና ባህል ተቋም በእንግሊዝኛ ምህፃሩ UNESCOበሰው ልጆች ወካይ የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ ተመዝግቧል። ማህበረሰቡ የሚገኝባቸው ኢትዮጵያ ፣ ጅቡቲ እና ሶማሊያ በጋራ በኢትዮጵያ አስተባባሪነት ባዘጋጁት ሰነድ ያቀረቡት የቅርስ ይመዝገብልን ጥያቄ አዎንታዊ ውሳኔ ያገኘው ዩኔስኮ ከቀናት በፊት በፓራጓይ መዲና ባካሄደው አመታዊ ጉባዔ መሆኑ ተገልጿል።

የቅርሱ በዓለም አቀፉ ተቋም መመዝገብ በብሄረሰቡ አባላት ዘንድ ደስታን ፈጥራል።  አቶ መሀመድ ሙሴ ጌሌ የሂሳ ዑጋዛዊ ምክር ቤት ቃል አቀባይ ሲሆኑ የብሄረሰቡ ያልተፀፈ ባህላዊ ህግ የሆነው "ሄር ሂሴ" በዩኔስኮ በመመዝገቡ "ደስታችን እጥፍ ድርብ" ነው ሲሉ ስሜታቸውን ለዶይቸ ቬለ ገልፀዋል።

ብሔረሰቡ ጠብቆ ያቆየው ባህላዊ ህግ በዓለም አቀፍ ደረጃ መመዝገቡ የተለያየ ጠቀሜታ እንዳለውም አቶ መሀመድ ተናግረዋል። የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ዑስማን በበኩላቸው ቅርሱ በዓለም አቀፉ ተቋም እንዲመዘገብ በርካታ ጥረቶች መደረጋቸውን አስታውሰዋል። አለም አቀፉ እውቅና ሌሎች ቅርሶችም እንዲጠበቁ እና ወደ እውቅና እንዲመጡ እድል ይፈጥራል ያሉት አቶ ኢብራሂም ከቅርሱ እውቅና ማግኘት ማግስት ባሉ ጥቂት ቀናት የተለያየ መነቃቃት መፈጠሩን ጠቁመዋል። የሶማሌ ሂሳ ማህበረሰብ ባህላዊ ህግ የሆነውን ሄር ሂሴ በዩኔስኮ ለማስመዝገብ ሲደረጉ በነበሩ ጥረቶች ዙርያ ዘገባዎችን ማቅረባችን ይታወሳል።

መሳይ ተክሉ

አዜብ ታደሰ

ዮሃንስ ገብረግዚአብሔር