በሰሜን እና ወሎ ያለ ዕድሜ ጋብቻ ያስከተለው ችግር
ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 17 2017በአማራ ክልል በመንግስትና በፋኖ ሀይሎች መካከል እየተካሄደ በሚገኘዉ ጦርነት ምክንያት ያለ እድሜ ጋብቻ በደቡብና ሰሜን ወሎ እየጨመረ ነዉ ተባለ። የትምህርት ተቋማት በጦርነቱ ምክንያት የተዘጉባቸዉ አካባቢዎች ላይ ያሉ ህፃናት በቤተሰቦቻቸዉ አስገዳጂነት እድሜያቸዉ ሳይደርስ እየተዳሩ መሆኑን የገለፁት የደቡብ ወሎ ዞን ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወይዘሪት ቤተልሄም ሰሎሞን መምሪያዉ ከተቀበላቸዉ 100 ያለእድሜ ጋብቻ ሊፈፀም ነዉ ጥቆማ ዉስጥ ማስቆም የቻለዉ ስምንቱን ብቻ ነዉ ይላሉ
ቡግና ወረዳ ከ79 ሺህ በላይ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ ይሻሉ
በሰሜን ወሎ ዞንም አሁን ላይ ጦርነት እየተካሄደባቸዉ ባሉ አካባቢዎች ባለሙያዎች ገብተዉ ሰራ መስራት ካለመቻል ባለፈ ያለእድሜ ጋብቻን ለመቆጣጠር የህግ አስከባሪ አካላት በቀበሌዎች ባለመኖራቸዉ ችግሩን ለመከላከል አስቸጋሪ አድርጎታል የሚሉት በመምሪያዉ የህፃናት መብት ደህንነት ማስጠበቅ ቡድን መሪ ናቸዉያለ እድሜ ጋብቻ ጎልቶ የሚታይበት የደቡብ ወሎዉ ከላላ ወረዳ በርካታ ትምህርት ቤቶች ዝግ ከመሆናቸዉ ጋር በተያያዘ ከአመት አመት ህፃናትን ያለ እድሜያቸዉ መዳር አየጨመረ እንደሆነ አቶ ሳኒ ሙህየ ይናገራሉ።
ህጻናትና እናቶችን ለከፋ ችግር የዳረገው የሰሜን ወሎ ቡግና ወረዳው የምግብ እጥረት
ወደ ትምህርት ቤት የሚመጡ ሴት ተማሪዎች ቁጥር መቀነስ ያሳሰበዉ የደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ ለሁለተኛ ዙር ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ ምዝገባ እያደረገ ቢሆንም ያለእድሜ ጋብቻ ፈተና መሆኑን አቶ አለምነዉ አበራ የዞኑ ትምህርት መምሪያ ሀላፊ ይገልፃሉ።አሁን ላይ በሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞን ያለእድሜ ጋብቻን በድብቅ መፈፀም እየተበራከተ በመምጣቱ ባለድርሻ አካላት ችግሩን ለመቅረፍ ርብርብ እንዲያደርጉም ተጠይቋል።
ኢሳያስ ገላው
ታምራት ዲንሳ
ኂሩት መለሰ