ትምህርትአፍሪቃ
«አስቸጋሪ ምርጫዎች» ድራማ
ዓርብ፣ መጋቢት 11 2012ማስታወቂያ
ይቺ ከተማ በተደጋጋሚ በጎርፍ እና በኮሌራ ወረርሽኝ ስትጠቃ ቆይታለች። በተለይ ደግሞ ገበሬዎች ተክል ተክለው የጎመራ አዝመራቸውን ለመሰብሰብ በሚፈልጉበት ዝናባማ ወቅት! ታዲያ ካለፉት ዓመታት አንስቶ የአየር ንብረቱ እጅጉን በመለወጡ ነገሮች ሁሉ ተባብሶባቸዋል። ለረዥም ዓመታትም ማኅበረሰቡ ለችግሩ ምንም መፍትሄ ሊያገኝ አልቻለም ነበር። በዚህ ዓመት ግን የሕዝቡን ሕይወት ለማሻሻል የገንዘብ ድጋፍ ተገኝቷል። ይህ ደግሞ እንደ ሃይማኖት እና ጓደኞቿ ካሪማ እንዲሁም ሲሳይ ላሉ የማኅበረሰቡ ወጣቶች አስደሳች ዜና ሆኗል። ሦስቱ ወጣቶች የዩንቨርስቲ ትምህርታቸውን ለአንድ ዓመት አቋርጠው በቅርቡ በተመመሰረተው የአባባቢ እና ጤና ጥበቃ ጽሕፈት ቤት በነፃ ሲያገለግሉ ሃይማኖት የማጋሪያ ከተማ ከንቲባን መጠራጠር ትጀምራለች። በእርግጥ ገንዘቡን ለህብረተሰቡ ጥቅም ማዋል ይፈልጋሉ? ወይስ ሌላ ነገር አለ? ለሶስቱ ጓደኛሞች የበጎ ፈቃደኝነት አመታቸው በፍጥነት ወደ ቅዠት ይቀየራል።
ደራሲ: ፒናዶ አዳማ ዋባ
ትርጉም: ልደት አበበ
ዝግጅት: ማንተጋፍቶት ስለሺ