1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዐማራ አጠቃላይ ጉባዔ በአትላንታ

ሰኞ፣ መጋቢት 2 2016

ዐማራው በአሁኑ ጊዜ ከሁሉም የከፋ ጥቃት እየረሰበት ነው ያሉት ሊቀመንበሩ፣ዓለም አቀፉ ማኀበረስብ ግን ለዚህ በደል ትኩረት አለመስጠቱን አመልከተዋል። በዚህ ላይም ውይይት መካሄዱንም አመልክተዋል።የመጀመሪያ የዐማራ አጠቃላይ ጉባኤ የዛሬ ዓመት ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ ዘንድሮ ደግሞ በዐማራ ማኀበር አስተናጋጅነት በአትላንታ ጆርጅያ ተካሄዷል።

https://p.dw.com/p/4dOls
የዐማራ አጠቃላይ ጉባኤ በአትላንታ
የዐማራ አጠቃላይ ጉባኤ በአትላንታምስል Tariku Hailu/DW

የዐማራ ማኀበራት ኅብረት ጉባኤ በአትላንታ

የዐማራ ማኀበራት ኅብረት

የዐማራ ማኀበራት ኅብረት በሰሜን አሜሪካ /ፋና/፣በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች የተቋቋሙ 17  ድርጅቶችና ሁለት የሙያ ማኀበራት ስብስብ ነው። ሁለቱ የሙያ ማኀበራት የዐማራ ማኀበር በሰሜን አሜሪካና የዐማራ ባለሙያዎች ማኀበር/ ዐምባ/ የተሰኙ ናቸው። ፌዴሬሽኑ የተቋቋመውም፣እንደ ጎርጎሮሳዊው ጊዜ አቆጣጠር በ2021 መሆኑ ተገልጿል።

የዐማራው ማኀበረሰብ አደረጃጀቶች

 

ፋና፣ በአትላንታ ባለፈው ቅዳሜ ያካኼደውን ጉባዔ አስመልክቶ ፕሬዚዳንቱ  አቶ የዚህዓለም መስፍን ለዶቼቬለ እንደተናገሩት ዓላማው "የዐማራው ኅብረተሰብ፣ የዐማራው ወገናችን በአካል ተገናኝቶ እንዲመክር፣በአካል ተገናኝቶ በልቡ የሰነቃቸውን ጥያቄዎች አሁን ባሉ ወቅታዊ ሁኔታዎች፣በዐማራው ትግል ዙሪያ ላይ ያሉብንን ፈተናዎች፣ በውስጥ በውጭ አደረጃጀቶቻችን መኻከል ያሉ ችግሮች ምንድናቸው ከሚለው ተነስተን በግል ከመታገል በድርጅት መታገል፣እና አደረጃጀቶች ምን ያህል ጠቀሜታ እንዳላቸው ለህብረተሰቡ የምናስረዳበት እና ከኅብረተሰቡም ደግሞ እነዚህን ተሞርኩዞ የሚቀርቡልንን ጥያቄዎችንም ለመመለስ ከእዛም ደግሞ ግብአቶችን ለመውሰድ ማለት ነው።"126ኛው የዐድዋ ድል በዓል በሰሜን አሜሪካ ተከበረ

ዐማራው በአሁኑ ሰዓት ከሁሉም የከፋ ጥቃት እየረሰበት ነው ያሉት ሊቀመንበሩ፣ዓለም አቀፉ ማኀበረስብ ግን ለዚህ በደል ትኩረት አለመስጠቱን አመልከተዋል። በዚህ ምክንያት ላይ ውይይት መካሄዱንም አመልክተዋል።"ዐማራው በቁጥር በጣም በዝቶ እያለ፣ዐማራው በአሁኑ ሰዓት ከሁሉም የከፋ በሚባል ደረጃ ጥቃት እየደረሰበት፣የዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ ለምንድነው ጆሮ ያልሰጠው ለምንድነው ለዚህ ትግል ያልሰጠው ከእኛ በኩል ምን መደረግ አለበት በሚለው ዙሪያ ላይ ከኅብረተሰቡ የሚመጡ ጥያቄዎችና ውይይቶችን እናደርጋለን።"ሊቀመንበሩ፣አሁን ባለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ መድረክ ውስጥ ዐማራ ሊኖረው የሚገባው ሚና ላይ ያተኮረ ምክክርም ነበር ብለዋል።

 

ፈተናዎችና የመፍትሔ ምክክሮች

 

የአማራ አጠቃላይ ጉባኤ በአትላንታ
የአማራ አጠቃላይ ጉባኤ በአትላንታምስል Tariku Hailu/DW

በዘንድሮ የዐማራ ማኀበራት ህብረት ጉባኤ ላይ ሌላው የፓናል ውይይት የተካሂደበት ርዕሰ ጉዳይ፣ በአሁኑ ወቅት በዐማራ ትግል ውስጥ አሉ ባሏቸው ፈተናዎች ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑን አቶ የዚህዓለም ይናገራሉ።  በአንዳንድ የዐማራ አደረጃጀቶች መኻከል የአካሄድ ልዩነቶች እንዳለ የጠቆሙት ሊቀመንበሩ፣  ይህንን ችግር ለመፍታት ከፍተኛ ጥረት መደረጉንና ወደፊት በታቀዱ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ምክክር መካሄዱን ተናግረዋል። ሌላው አበይት የመወያያ አጀንዳ የአደረጃጀቶችን ጥቅም የተመለከተው መሆኑን አቶ የዚህዓለም ለዶይቸ ቨለ ገልጸዋል። 

"በግል ሆኖ ከመጮህ ተደራጅቶ መስራት እንዴት እንደሚጠቅም፣ ከእዛም አልፎ ሚዲያዎች ከድርጅቶች ጋር ተዋቅረው እንዴት መስራት አለባቸው፣ የሚዲያዎችና ድርጅቶች አንድላይ ሲቀናጁ የሚያመጣው ውጤት ምንድነው በሚለው ዙሪያ ላይ ደግሞ ከኅብረተሰቡ ጋር ውይይት ይደረጋል ጥያቄና መልሶች በዚህ ዙሪያ ይመለሳሉ።"የኢትዮጵያና ኤርትራውያኑ ተቃውሞ በ CNN መሥሪያ ቤት

 

ከጉባዔው የሚጠበቁ ውጤቶች

"በኅብረተሰቡ ዙሪያ ያሉ ጥያቄዎች ምንድናቸው? አብዛኛው ኀብረተሰብ ምን እንዲደረግ ነው የሚፈልገው የሚለውን ግብዓት መውሰድ ከእነዛ ላይ ተነስተን ስትራቴጂ መንደፍ ማለት ነው እና  ከዚህ ዝግጅት የምንጠብቀው፣ በውይይት ከማኀበረሰቡ የሚመጡ ስሜቶችን መውሰድ ነው ለእኛ ግብዓት ሆኖ በአደረጃጀቶች ላይ መስተካከል  ያለባቸው ነገሮች ካሉ ከጥያቄዎች በእኛ በኩል ይህን ዝግጅት ካዘጋጀው ከ17 ማኀበራት በኩል ከኅብረተሰቡ ያለውን ስሜት መውሰድ፣ኅብረተሰቡ ምን ይፈልጋል የሚለውን፣አንዳንድ ብዥታዎች ደግሞ ካሉ ይህን የማጥፋትና ዕድል የማግኘትና ከኅብረተሰቡ ጋር ፊት በፊት መገናኘትና  መወያየቱ ነው ትልቁ ነገር።" በማለት አቶ የዚህዓለም ከጉባዔው የሚጠበቁትን አስረድተዋል።

የመጀመሪያ የዐማራ አጠቃላይ ጉባኤ፣የዛሬ ዓመት ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ ነበር የተካሄደው፤ ዘንድሮ የኅብረቱ አባል በሆነው የዐማራ ማኀበር በጆርጂያ  አስተናጋጅነት አትላንታ ላይ ተካሄዷል።

ታሪኩ ኃይሉ 

ኂሩት መለሰ

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር