ትምህርትአፍሪቃ
«የጥላቻ እና የፍቅር ቃላት» ድራማ
እሑድ፣ የካቲት 29 2012ማስታወቂያ
በሀገሯ የጎሳ ግጭት እየጨመረ በመሄዱ አፍሪካዊቷ ወጣት ጋዜጠኛ ጁን የጥላቻ ንግግርን ለመዋጋት ወስናለች። ከአመታት የስደት ጉዞ በኋላ ፖለቲከኛ ባንኩ ወደ አገሯ ማጋንጌ ስትመለስ በተዘጋጀላት የአቀባበል ሥርዓት ላይ ድንገት በአደገኛ ሁኔታ በስለት ተወግታለች። ይህ ደግሞ እሷ በምትወክለው ጎሳ እና በስልጣን ላይ ባለው እና የኢኮኖሚውን የበላይነት በያዙት የጎሳ ግጭት እንደገና እንዲነሳ አድርጓል። የሁለቱም ጎሳዎች አባል የሆነችው ወጣት ጋዜጠኛ ጁን የጥላቻ ንግግሮችን እየታገለች ነው ። ይሳካላት ይሆን? ። ለመሆኑ በባንኩ ላይ ጥቃቱን የፈጸሙት እነማን ናቸው? የደሬምባ ማህበረሰብ እንደሚለው ፕሬዝዳንቱ በእርግጥ በዚህ ተሳትፈዋልን? ኢንስፔክተር ኦፓንዴ ያገረሸው የጎሳ ግጭት ወደ እርስበርስ ጦርነት ከመሸጋገሩ በፊት ጉዳዩን ለመፍታት ከጊዜ ጋር ሩጫ ይዘዋል።
ደራሲ: ክሪስፒን ምዋኪዲዮ
ትርጉም: እሸቴ በቀለ
ዝግጅት: ማንተጋፍቶት ስለሺ