የአውሮጳ ኅብረት የወጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባና ዉሳኔዎች
ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 8 2017የአውሮጳ ኅብረት የወጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የ 2024 ዓመት የመጨረሻ ስብሰባና ያሳለፋቸው ውሳኔዎች
የሀያ ሰባቱየአዉሮጳ ኅብረት አባል አገሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የአውሮጳውያኑን 2024 ዓመት የመጨርሻ ስብሰባ ብራስልስ ላይ አካሂደው ውሳኔዎችን አሳልፈዋል። ቀድሞ የእስቶኒያ ጠቅላይ ሚኒስተር በነበሩት አዲሷ የኅብረቱ የውጭ ጉዳይ ሀላፊ ወይዘሮ ካያ ካላስ የተመራው ስብሰባ የተወያየውው፤ በዋናነት በዩክሬን፣ መካከለኛው ምስራቅና የጆርጂያ ሁኔታ ላይ እንደነበር ተገልጿል። ሚኒስትሮቹ በስብሰባቸው ማጠቃለያ በሩሲያ ላይ ለ15ኛ ግዜ በግለሰቦችና የኢኮኖሚ አውታሮች ላይ የማዕቀብ ውሳኔዎችን እንዳሳለፉና ለዩክሬን የሚሰጠውን ወታደራዊና የፋይናንስ እርዳታም አጠናክረው ለመቀጠል የተስማሙ መሆኑም ተገልጿል። በመካከለኛ ምስራቅ ላይም ሚኒስትሮቹ በጋዛ የተኩስ ማቆም ስምምነት እንዲደረግና የሰባዊ እርዳታ እንዲገባ ጥሪ ማድረጋቸው ታውቋል። በሶሪያ ሁሉ አቀፍና ሰላማዊ የሽግግር ስራት እንዲኖር ከአካባቢውና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር የሚደረገው ጥረት እንዲቀጥልም ወሰነዋል።
ለዩክሬን የሚስጠው ወታደራዊ ድጋፍ ቀጣይነት
ወይዘሮ ካላስ በስብሰባው መጨረሻ በሰጡት ጋዜጣዊ መገልጫ የተጠቀሱትን የሚስትሮቹን ውሳኔዎች አብራርተዋል። ዩክሬን የሩሲያን ወረራ ለመመከት እያደረገችው ያለውን ጦርነት ከመርዳት ውጭ አማራጭ የለም በማለትም፤ ኅብረቱ ድጋፉን አጠናካሮ እንዲቀጥል ሚኒስትሮቹ የወሰኑ መሆኑን አስታውቀዋል። ። “ ዩክሬንን መደገፋችን ይቀጥላል። እስከዚህ የክረምት ወቅት መጨረሻ ድረስ ኅብረቱ 75 ሺ የዩክሬን ወታደሮችን ያሰለጥናል። በዚህ ወር ብቻ ኅብረቱ ለዩክሬን 4.2 ቢዮን ይሮ ያቀረበ ሲሆን፤ ከሚቀጥለው የጥር ወር ጀምሮም በየወሩ 1.5 ቢሊዮን ይሮ የሚለግስ ይሆናል” ብለዋል።
የሶሪያ የሽግግር ስራት ሊመሰረትባቸው የሚገባ መርሆዎች
ወይዘሮ ካላስ በሶርያ ጉዳይ ቀደም ሲል ወደ መካከለኝው ምስራቅ በመጓዝ ከአረብ አገሮች፤ ቱርክና አሜሪካ ጭምር የሶሪያ የሽግግር ሂደትበምን መርሆዎችላይ መመስረት እንዳለበት እንደተወያየዩና የጋራ አቋም እደተወሰደ አውስተው፤ ሚኒስትሮቹም በእነዚህ መርሆዎች ላይ የተስማሙ መሆኑን ገልጸዋል። አስፈላጊና መሰረታዊ ያሏቸውን መርሆዎችን ሲያብራሩም፤ “ አገራዊ አንድነትና ለዑአልዊነት፣ ተጠያቄነት፣ አካታችነትና በተለይም የአናሳ ህዝቦችንና የሴቶች መበት መከበርና መጠበቅ ዋና ዋናዎቹ ናቸው” በማለት ሂደቱም በሶሪያውያን የታቀፈና የሚመራ እንዲሆን እንደታመነበት አስታውቀዋል። የሚቋቋመው የሽግግር መንግስት በሶሪያ ያሉትን የሩሲያ የጦር ሰፈሮች እንዲዘጋ ሊጠየቅና ለምራባውያን ድጋፍና እውቅናም እንደቅድመ ሁኔታ ሊቀመጥ እነደሚገባው የሚጠይቁ ሀሳቦች እንደተነሱ በመጥቀስም ጉዳዩ በመሪዎች ደረጃ ውይይት ሊደረግበት እንደሚችል ጠቁመዋል።
አክለውም የውጭ ጉዳይ ሀላፊዋ ከእንግዲህ በሶሪያ አክራሪነት ቦታ ሊኖረው እንደማይገባና የኅብረቱ ልዑክ ባሸር አሳድን ካስወገዱት ሀይሎችቾ ጋር ለመነጋገር ወደ ደማስቆ መሄዱን አንስተዋል። ሆኖም ግን በተለይ በአሸባሪነት ተፈርጆ ከነበረውና ቀደም ሲል ካአልቃይዳ ጋር ግንኑነት ነበረው ከሚባለው ያሳድን መንግስት ከገለበጠው ድርጅት ሃያ ታህሪር አል ሻምና መሪው አህመድ አልሻራ ጋር ይፋዊ ግንኑነት ለመመስረት ተግባራዊ እርምጃዎችን እንደሚጠብቁ አስታውቀዋል።
በጆርጂያ ባለስልጣኖች ላይ የተላለፈው ውሳኔ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ ወደኅብረቱለመግባት ታጭተው ከነበሩት አንዷ በነበረችው ጆርጂያ፤ በቅርቡ የተካሄደውን ምርጫ ትከትሎ በተፈጠረው ቀውስ ምክኒያት በተቃዋሚዎችና ሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አውግዘዋል። የውጭ ጉዳይ ሀላፊዎ በጆርጂያ ባለስልጣኖች ላይ ማቀብ እንዲጣል የውሳኔ ሀሳብ አቅርበው የነበር ቢሆንም በሁለት አባል አገሮች ተቃውሞ ምክንያት ውሳኔው ውድቅ እንደሆነ፤ ሆኖም ግን በባለስጣኖቹ ላይ የነጻ ዲሎማሲያዊ ቪዛ ክልከላ እንዲጣል የተወሰነ መሆኑ ተገልጿል።
የውጭ ጉዳይ ሀላፊዋ ቀጣይ ፈተና
አዲሷ የውጭ ጉዳይ ሀላፊ ወይዘሮ ካያ ካላስ ጠቅላይ ሚኒስትር በነበሩትት ወቅት በተለይ በሩሲያ ላይ ጠንካራ አቁም በማራመድ የሚታወቁ ሲሆን በመካከለኛው ምስራቅ ላይ ግን የቀድሞውን የውጭ ጉዳይ ሀላፊ ጆሴፕ ቦርየልን ያህል ላይሆኑ ይችላሉ በመባል ይጠቀሳሉ። ይሁን እንጂ የኅብረቱ የውጭ ጉዳይ ውሳኔዎች በአብዛኛው የሁሉንም አባል አገሮች ስምምነት የሚጠይቁ በመሆናቸውና አባል አገሮች ደግሞ በበርክታ ጉዳዮች ልዩነቶች ያሏቸው በመሆኑ፤ ወይዘሮ ካላስ በዩክሬንም ሆነ በመካከለኛው ምስራቅና ሌሎች ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ያባል አገራቱን አቋም አመቻምቾ ማስቀጥሉ ከባድ ፈተና ሊሆንባቸው እንደሚችል ነው ታዛቢዎች የሚናገሩት
ገበያው ንጉሴ
አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ